This job listing has expired

Applications are no longer being accepted for this position.

Wolaita Sodo University logo

ፕሬዚዳንት

Wolaita Sodo University • Wolaita Sodo

On-siteFull-timeWolaita SodoMid Level

Experience

Mid Level

Salary

Not specified

Posted

about 1 month ago

Deadline

Expired (11 days ago)

Job Description

የስራው መግለጫ

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የፕሬዚዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሠረት የፕሬዚዳንት ክፍት አመራርነት መደብ ላይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ልምድ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድረው መመደብ መሾም/መሰየም ይፈልጋል፡፡

የስራ መስፈርቶች

የትምህርት ደረጃ፡

  • 2ኛ ዲግሪና ከዚያ የረዳት ፕሮፌሰርነት የአካዳሚክ ማዕረግ ያለው/ላት

የስራ ልምድ፡

  •  ቢያንስ ሁለተኛ ድግሪ ኖሮት የረዳት ፕሮፌሰርነት ወይም በህክምና ሙያ ስፌሻሊቲና በዚህ ደረጃ አቻ የሆነ የአካዳሚክ ማዕረግ ያለው/ያላት፤
  • በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው መደበኛ መሪህ ቢኖርም ሁለተኛ ድግሪ ኖሯት ከከፍተኛ ተቋም ለምትመጣ ሴት እጩ ተወዳዳሪ የአካዳሚክ ማዕረግ (ረዳት ፕሮፌሰርነት) ሳይጠበቅባት ለፕሬዚዳንትነት የሥራ መደብ ልትወዳደር ትችላለች።
  • ዝቅተኛው የሥራ ልምድ በፕሬዚዳንትነት 2 ዓመት ወይም በምክትል ፕሬዚዳንትነት 3 ዓመት ወይም በኮሌጅ ዲንነት 3 ዓመት ያገለገለ መሆን ይኖርበታል።
  • ከኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚመጣ ተወዳዳሪ በአመራርነት የስራ መደብ በሰራበት መስሪያ ቤት የመራው የሠራተኞች ብዛት ያመነጫውና ያስተዳደረው የበጀት መጠን ከሚወዳደርበት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል።
  • ከኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሚመጡ እጩ ተወዳዳሪዎች የሚጠበቀው ዝቅተኛ የስራ ልምድ በበላይ አመራርነት ቢያንስ 5 ዓመት፡ በከፍተኛ አመራርነት ቢያንስ 5 ዓመት፤ በዋና እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ወይም በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እና ከዚህ ጋር አቻ በሆኑ የኃላፍነት ቦታዎች ላይ ቢያንስ 8 ዓመት አገለግሎት የሰጠ/የሰጠች መሆን ይኖርበታል/ባታል።

ብዛት: 1

ጾታ፡ አይለይም

ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅም፡ የኃላፊነት አበል፤ የአኑዋላይዜሽን እና የደመወዝ 20%፤ የቤት አበል

ዋና ዋና ኃላፊነቶች

  • የታካሚዎችን የራዲዮሎጂ ምርመራ ፍላጎት መገምገም
  • ኤክስሬይ፣ CT፣ MRI እና አልትራሳውንድ ምስሎችን መመርመርና መተንተን
  • የምስል ምርመራ ውጤቶችን መተርጎምና ሪፖርት ማዘጋጀት
  • የበሽታ ወይም የጉዳት ምልክቶችን በምስል ምርመራ መለየት
  • አስፈላጊ ሲሆን ተገቢውን የራዲዮሎጂ ምርመራ መምረጥና ማዘዝ
  • የምርመራ ውጤቶችን ከሐኪሞችና ከሌሎች የጤና ባለሙያዎች ጋር መወያየት
  • የታካሚ መዝገቦችንና የራዲዮሎጂ ሪፖርቶችን በትክክል መመዝገብ

የማመልከቻ መመሪያ

አመልካቾች ሕይወት ታሪክ (CV) እና የትምህርት ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ፣ የሥራ ልምድ እና የአመራርነት አገልግሎት ማረጋገጫ ሰነድ እና የዩኒቨርሲቲ መምህር ከሆኑ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ያሳተሟቸውና የምርምር ስራዎች አርትኦት እና የታተሙ ሳይንሳዊ ጽሑፎች አርትክሎች ጋር በመያዝ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 28 እንዲሁም አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ በሚገኘው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ ቤት በአካል በመቅረብ ማመልከት ይችላሉ፡፡

ማስታወሻ፡ ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ የተቋሙን ራዕይ እና ተልዕኮ የሚያስፈጽም ስትራቴጅክ እቅድ በማስተማሪያ ቋንቋ አዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል። በምክትል ፕሬዚዳንትነት ለተከታታይ ሁለት ተርም ያገለገለ ሰው ለፕሬዚዳንትነት የሥራ መደብ መወዳደር ይችላሉ። ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከአካዳሚክ ስታፍ ለሚመጣ እጩ ተወዳዳሪ የረዳት ፕሮፌሰርነት እና ከዚያ በላይ የአካዳሚክ ማዕረግ ያለው መሆን አለበት። በአንድ ተቋም ውስጥ በፕሬዚዳንትነት ወይም በምክትል ፕሬዚዳንትነት ማዕረግ በመሥራት ላይ ያለ አመራር፣ በራሱ ተቋም በሚወጡ ተመሳሳይ የውድድር መደቦች ላይ መወዳደር አይችልም። ሆኖም በሌሎች ተቋማት በሚወጡ ክፍት የአመራር መደብ ማስታወቂያዎች ላይ መወዳደር ይችላል። ለወጣው ክፍት የአመራር ስራ መደብ የሚያመለክቱ ኢትዮጵያዊ/ት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ/ት የሆነ/ች እና የጡረታ ጊዜው/ዋ ሳይደርስ ሙሉ ስድስት ዓመት ማገልገል የሚችል/የምትችል መሆን አለበት/ባት፡፡ እጩ ተወዳዳሪው/ዋ በከባድ ወንጀሎች እና ከባድ የዲስፒሊን ጉድለት ክስ ወይም ጥፋት የሌለበት/ባት መሆን አለበት/ባት። የምልመላ ውጤት፤ የቃል ፈተና ጊዜ እና ቦታ በተመዘገቡበት የምዝገባ ማዕከል በማስታወቂያ ሰሌዳ ይገለፃል። ሰነዶች በሙሉ ስካን የተደረጉ ፒዲኤፍ ፋይሎች መሆን ይኖርባቸዋል

ለበለጠ መረጃ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ በስልክ ቁጥር 0461800602 ወይም በአዲስ አበባ ባለዉ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር +251912881430 /+251938362357 ይደውሉ፡፡

የኢሜይል አድራሻ - mgmtrecruitmetawsu.edu.ef

የተቋሙ ፖ.ሣ.ቁ 138

Requirements

Required Skills

write work-related reportspresent reportsliaise with educational staffmonitor educational developmentsrepresent the organisation

Level

Mid Level

Location

Wolaita Sodo

How to Apply

አመልካቾች ሕይወት ታሪክ (CV) እና የትምህርት ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ፣ የሥራ ልምድ እና የአመራርነት አገልግሎት ማረጋገጫ ሰነድ እና የዩኒቨርሲቲ መምህር ከሆኑ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ያሳተሟቸውና የምርምር ስራዎች አርትኦት እና የታተሙ ሳይንሳዊ ጽሑፎች አርትክሎች ጋር በመያዝ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 28 እንዲሁም አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ በሚገኘው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ ቤት በአካል በመቅረብ ማመልከት ይችላሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ 0461800602(ወላይታ ሶዶ) / +251912881430 / +251938362357 (አዲስ አበባ)