This job listing has expired
Applications are no longer being accepted for this position.
Experience
Junior
Salary
Not specified
Posted
14 days ago
Deadline
Expired (6 days ago)
Job Description
ድርጅታችን ኤስ ኤን ኤፍ ዲ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በምግብ ዝግጅት ረዳት ሼፍ ሰራተኞችን ብስራተ ገብሬል (ሙልሙል ዳቦ ቤት) ቅርንጫፍ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
የስራ መስፈርቶች
የትምህርት ደረጃ ፡- በተዛማጅ የትምህርት መስክ ዲፕሎማ ያለው/ላት
የስራ ልምድ፡- ታዋቂ ሬስቶራንት ዉስጥ በፋስት ፉድ ከሁለት አመት (2) በላይ የሰራ/የሰራች
ብዛት ፡ 4/አራት/
ጾታ፡ አይለይም
ደመወዝ፡- በስምምነት
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
የምግብ ዝግጅት ስራዎችን ለዋናዉ ሼፍ በማገዝ ማከናወን
የምግብ ዝግጅት ቦታዎችን ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን ንጹህ ማድረግ
የደንበኞችን የምግብ ትዕዛዝ በፍጥነትና በትክክል ማዘጋጀት
የምግብ ንጽህናና የጤና ደህንነት መመሪያዎችን መተግበር
የምግብ ግብዓቶችን አጠቃቀም መቆጣጠርና ብክነትን መቀነስ
የምግብ ግብዓቶች ክምችት ሲያንስ ለኃላፊዉ ሪፖርት ማድረግ
የምግብ ጥራት እንዲጠበቅ የሚያስፈልጉ ሂደቶችን መከተል
የግሉንም ሆነ የስራ ቦታ ንጽህና መጠበቅ
የድርጅቱን የስራ መመሪያ ማክበር
የጋራ ስራዎችን /team work/ በፈቃደኝነት ማከናወን
የማመልከቻ መመሪያ
ከላይ የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን በኢሜል አድራሻችን mulmulhr@gmail.com ወይም የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ ሃያ ሁለት ቅርንጫፍ በሚገኘው ዋናው ቢሮ በስራ ቀናት ከሰኞ - አርብ ከ2፡00 እስከ 11፡00 እና ቅዳሜ እስከ 6፡00 በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማስታወሻ፡ አመልካቾች ተያዥ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
Requirements
Required Skills
Level
Junior
Location
Addis Ababa