This job listing has expired
Applications are no longer being accepted for this position.

Experience
Entry Level
Salary
ETB 8K - 8K
Posted
18 days ago
Deadline
Expired (14 days ago)
Job Description
የስራ መስፈርቶች
የትምህርት ደረጃ: በቋንቋ (አማርኛ ፣ እንግሊዝኛ ፣ የጽህፈትና ቢሮ አስተዳደር ሴክሬታሪያ ሳይንስና ኦፊስ ማኔጅመንት፣ በኢንፎርሜሽን ቴከኖሎጂ፣ አይሲቲ ፣ አይቲ፣ ኢንፎርሜሽን ሳይንስ ፣ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ፣ አይቲ ሳፖርት ሰርቪስ ፣ ኢንፎርሜሽን ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፣ አይሲቲ ሰፖርት እና ሲስተም ሰርቪስ ( ፣ ሴክሬታሪ ቴከኖሎጂ ፣ ኮምፒውተራይዝድ ሴክሬታሪያል ሳይንስ እና ኦፊስ ማኔጅመንት ፣ ካስተመር ኮንታክት እና ሴክሬታሪያል ኦፕሬሽን ፣ ቴከኖሎጂ ሲስተም እና ኦፊስ ማኔጅመንት ፣ አድሚኒስትሬቲቭ ኦፊስ ማኔጅመንት ቴክኖሎጂ ሲስተም ኦፊስ አድሚኒስትሬሽ፤ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አሲስታንት ፣ ዳታቤዝ አድሚኒስትሬሽን ኮሌጅ ዲፕሎማ ወይም የቴከኒክና ሙያ በደረጃ 3 /10+3/ የተመረቀ/ች እና የCOC ምዘና ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው/ላት
የስራ ልምድ: 0 ዓመት
ብዛት: 1
ደመወዝ፡ 8478
ደረጃ፡ VII
የቅጥር ሁኔታ፡ በኮንትራት/ ለአንድ ዓመት/
የመደብ መታወቂያ ቁጥር፡ 6.3/ቤተ-327
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
መጻሕፍትንና ሌሎች የመረጃ ሰነዶችን በአግባቡ ማስቀመጥና ማደራጀት
ለአንባቢዎች የሚፈልጉትን መጻሕፍትና የመረጃ ምንጮች እንዲያገኙ እገዛ ማድረግ
መጻሕፍትን ለአንባቢዎች ማበደርና የተመለሱትን መረከብ
የተበደሩና የተመለሱ መጻሕፍትን መዝገብ መያዝ
የመጻሕፍትን ዝርዝርና የአንባቢዎችን መረጃ በአግባቡ መመዝገብ
የቤተመጻሕፍቱን ንብረቶች መጠበቅና የተበላሹ ወይም የጠፉ መጻሕፍትን ለኃላፊው ማሳወቅ
የማመልከቻ መመሪያ
አመልካቾች የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃችሁን ዋናውን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በመያዝ ሬዲዮ ፋና ፊት ለፊት ወይም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በታችኛው በር ፊት ለፊት ባለው አስፋልት በኩል በሚገኘው በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በቀድሞ ስያሜው ወመዘክር የሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 112 በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
ማስታወሻ፡ አመልካቾች የሚያቀርቡት የስራ ልምድ ስርዝ ድልዝ የሌላቸውና በግልፅና በጥንቃቄ የተጻፉ መሆን ሲኖርባቸው የሠሩበት የሥራ መደብ መጠሪያ ከመቼ እስከ መቼ እንደሠሩ ቀን ወር ዓ.ም በግልፅ መግለፅ አለባቸው የሥራ መደቡ ላይ ሲሠሩ በየሥራ መደብ በየወሩ ወይም በሌላ ሁኔታ በቋሚነት ሲከፈል የነበረውን የደመወዝ መጠን የሚገልጹ የአሰሪዎችን ሙሉ ስም ፊርማ የሥራ ደረጃና የተቋሙ ማህተም የታተመበት፤ ማስረጃዎቹ የተሰጡበት ቀን ወርና ዓመተ ምህረት እንዲሁም ፕሮቶኮል ቁጥር የያዙ በሕጉ መሠረት የሥራ ግብር መከፈሉን መግለፅ ይኖርበታል ።
በግል ተቋም የሚመጡ የሥራ ልምዶች የሥራ ግብር ለመከፈሉ ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ የመንግሥት አካል ስለመከፈሉ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን +251115530505 ይደውሉ፡፡
Requirements
Required Skills
Level
Entry Level
Location
Addis Ababa