This job listing has expired
Applications are no longer being accepted for this position.

Experience
Junior
Salary
Not specified
Posted
18 days ago
Deadline
Expired (5 days ago)
Job Description
የስራው መግለጫ
የመኪና ነጂ ደረጃ አንድ ዋና ተግባር ደብዳቤዎችን፣ መልዕክቶችንና ሌሎች ዕቃዎችን ወደ ቢሮ ማድረስ ወይም ወደ ተለያዩ ድርጅቶችና መሥሪያ ቤቶች መላክ ሲሆን፣ በተጨማሪም የድርጅቱን የአገልግሎት ተሽከርካሪዎች በደህንነትና በተገቢው ሁኔታ ማሽከርከር፣ የተሽከርካሪውን ዝግጁነት መጠበቅ እና አነስተኛ ጥገናዎችን ማከናወን ነው።
የስራ መስፈርቶች
የትምህርት ደረጃ፡
በቀድሞው 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች ወይም በአዲሱ 10ኛ ክፍል፣ 10+1 በአውቶ ሜካኒክ ወይም በኦቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች
ደረጃ 4/ደረጃ 3 መንጃ ፈቃድ ወይም ሕዝብ 1/ሕዝብ 2 መንጃ ፈቃድ ያለው/ያላት
የሥራ ልምድ
ሁለት (2) ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት።
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
የትራፊክ ሕጎችንና የመንገድ ላይ ሥነ ሥርዓቶችን በማክበር ተሽከርካሪውን ማሽከርከር
በክልሉ ትራንስፖርት መገናኛ ቢሮ በተፈቀደው ሕጋዊ መንገድ የሚመደብለትን/የሚመደብላትን ተሽከርካሪ ብቻ ማሽከርከር
በሚመለከተው ኃላፊ ወይም አለቃ ትእዛዝ መሠረት የድርጅቱን የአገልግሎት መኪናዎችና ሌሎች የባንኩን ተሽከርካሪዎች የማሽከርከር አገልግሎት መስጠት
ደብዳቤዎችን፣ መልዕክቶችንና ሌሎች ዕቃዎችን በታዘዘው መሠረት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማድረስ
በየቀኑ የሚጓዘውን የኪሎ ሜትር ርቀት በትክክል መመዝገብ
የዕለት ተዕለት ሥራውን/ሥራዋን ከመጀመሩ/ከመጀመሯ በፊት የተሽከርካሪውን ዝግጁነት መፈተሽ። ይህም የዘይት መጠን፣ የውሃ መጠን፣ የፍሬን ደህንነት፣ መብራቶችና ሌሎች አስፈላጊ ክፍሎችን ማረጋገጥን ይጨምራል
ተሽከርካሪውን በንጽህና በመጠበቅ ሁልጊዜ ለሥራ ዝግጁ ማድረግ
አነስተኛ ጥገናዎችን ማከናወን፤ ለምሳሌ ስፓርክ ፕላጎችን ማጽዳት፣ ካርቦሬተርን ማስተካከልና አንዳንድ የተበላሹ ክፍሎችን መጠገን
አደጋዎች ወይም ያልተለመዱ አጋጣሚዎች ሲከሰቱ ለሚመለከታቸው ኃላፊዎችና ለቅርብ አለቃው/አለቃዋ በፍጥነት ማሳወቅ
ተሽከርካሪው ጋራዥ ሲገባ የጥገና ሥራዎችን በመከታተል ጥገናው በሚፈለገው ደረጃና በአጥጋቢ ሁኔታ መከናወኑን ማረጋገጥ
ለባንኩ ሥራዎች የተረከባቸውን/የተረከበቻቸውን ዕቃዎችና መሣሪያዎች በጥንቃቄ መያዝና በአግባቡ መጠቀም
ከጊዜ ወደ ጊዜ በቅርብ አለቃው/አለቃዋ በሚሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ማከናወን
የማመልከቻ መመሪያ
አመልካቾች የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ማመልከት ይችላሉ፡፡ THIS LINK
Requirements
Required Skills
Level
Junior
Location
Addis Ababa